Fana: At a Speed of Life!

ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጉ የግብርና ምርቶች ዋጋ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጉ የግብርና ምርቶች ጥራት ፣መጠን እና ዋጋ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሔደ ነው፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲያሳካ የግብዓት አቅርቦት እጥረት እና የጥራት ችግሮችን በመለየት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግና ቅንጅታዊ አሠራርን ለመፍጠር ነው ውይይቱ እየተካሔደ የሚገኘው፡፡

የግብዓት አቅርቦት ጥራትና የገበያ ትስስር ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩ ሚናቸው የላቀ ቢሆንም÷ ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጉየግብርና ምርቶች በሚፈለገው ጥራት መጠንና ዋጋ ማቅረብ ላይ ባሉ ውስንነት መኖሩ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በዚህም ከዘርፉ እየተገኘ ያለው የኢኮኖሚ ጥቅም አነስተኛ መሆኑን ነው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን ሙሐመድ የተናገሩት፡፡

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው መሰረት ላለፉት አራት ዓመታት አበረታች የኢኮኖሚ ዕድገት መመዝገቡንም አስታውሰል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን የግብዓት አቅርቦት እጥረት እና የጥራት ችግሮች በመቅረፍ የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በማስጀመር በርካታ ተስፋ ሰጭ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግሩ በግብዓት አቅራቢዎች እና በአምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል የገበያ ትስስር መፍጠር እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒቴስር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.