Fana: At a Speed of Life!

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከዳያስፖራው 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ከላከው የውጭ ምንዛሬ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በተጨማሪም ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ተቀማጭ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምንዛሬው የተገኘው ከሁለት ሺህ በላይ የዳያስፖራ አካውንቶች ተከፍተው መሆኑንም ኤጀንሲው ጠቁሟል፡፡

በ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዳያስፖራው በፐብሊክና ዲጂታል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በሐብት ማሰባሰብ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ማኔጅመንት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙንም ገምግሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.