Fana: At a Speed of Life!

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ክፍት መሆናቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ክፍት መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በኢፌዴሪ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ÷ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት መደረጉንኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት÷ በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ፤ በሁመራ በኩል ሸራሮ፣ ሽረ – አክሱም -ዓድዋ፤ በጎንደር -ዓዲ ዓርቃይ – ማይጸብሪ- ሽረ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን÷ በሁመራ በኩል ሸራሮ- ሽረ- አክሱም -ዓድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል ሶስቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.