Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆኗል።

መማሪያው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በተገኙበት ነው ይፋ የሆነው።

መማሪያው በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ አካል ሊጠቀምበት እንደሚችል የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ መተግበሪያው በትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የበለጠ በማጠናከር በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የተማሪዎችን የመረዳት አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

አያይዘውም የትምህርት ስርአቱ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ የመማሪያና ማስተማሪያ ቋንቋ በአብዛኛው እንግሊዝኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመረዳት የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል::

ከተለያዩ ሀገራት በጎ ፈቃደኛ የእንግሊዘኛ መምህራንን እና የዳያስፖራ አባላትን ወደ ሀገር ቤት በማስመጣት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለማሰማራት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ መተግበሪያው ይፋ መሆኑ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል።

የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው ትውልድን የመገንባት ሃላፊነት የጋራ በመሆኑ መማሪያው ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋችን ማህበራዊ ሃላፊነታችን የምንወጣበት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል::

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎች ኢትዮ ቴሌኮም እንደሚደግፍ ተናግረዋል።

መማሪያው የመማሪያ መጽሐፍትን ጨምሮ የተለያየ ይዘት ያላቸው የእንግሊዝኛ ትምህርቶችን በተለያየ የክፍል ደረጃ እንደሚቀርቡበት ተገልጿል።

ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ቀሪው የማህበረሰብ ክፍልም የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለመማርና ለማሻሻል እንዲጠቀምበት ጥሪ ቀርቧል::

አገልግሎቱን መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በሚከተለው አድራሻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.