ወሎ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 394 ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 394 ተማሪዎች አስመረቀ።
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በክረምት፣ ተከታታይና በርቀት ትምህርት የተከታተሉ ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በኢንጅነሪንግ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 332 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።
በምርቃት ሥነ ስርአቱ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በዘሩ ከፈለኝ