የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት ለተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

By Shambel Mihret

November 12, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት ለተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ነገ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ  ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ መለው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ውድድሩ ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ድረስም የሚከተሉት መንገዶች ለተሸከርካሪ ዝግ ይሆናሉ

በዚህም ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ፣ በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ፣ ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ፣ ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ፣ ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ፣ ከአፍሪካ ህብረት ወደ ቡልጋሪያ፤

ከትምባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል፣ ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር፣  ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር፣ ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር፣ ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር፣ ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፤

ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በውድድር መስመር  ግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡