የመዲናዋ አመራሮች በከተማው በሚተገበረው የሌማት ትሩፋት ዕቅድ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በከተማው በሚተገበረው የሌማት ትሩፋት ዝርዝር ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ይህን ወሳኝ ተግባር ለማሳካት እንችላለን ብለን አምነን መነሳት አለብን ብለዋል፡፡
ይህንንም እንደሀገር በአረንጓዴ ዐሻራ እና በስንዴ ልማት ማድረግ እንደምንችልና እንደምናሳካ አረጋግጠናል ነው ያሉት፡፡
የሌማት ትሩፋቱ በሕዝብ ንቅናቄ እንደሚራ ጠቁመው÷ ሕዝቡም አጠገቡ ያለውን አቅም እየተጠቀመ በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ አቅም ወደ ውጤት መቀየር ይኖርበታል ብለዋል፡፡
እንቀየር ብለን ከተነሳን ጥቂቷን ነገር ወደ ውጤት እየቀየርን መሄድ ይኖብናል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፡፡
ዋናው ጉዳይ የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ፣ የሚቋቋም ኢኮኖሚ መገንባት እና ሌማታችን ከራሳችን አልፎ ለጎረቤቶቻችን የምናጋራ እንዲሆን ነው ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ዋናው ትኩረቱ የሕዝቡን ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይር ሥራ መሥራት መሆኑንም ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሌማት ትሩፋት ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ጥቅምት 27 በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!