የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Alemayehu Geremew

November 12, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

የግጭት አደጋው ያጋጠመው ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ሲሆን÷ ከኮምቦልቻ ወደ አዲስ አበባ እና ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ በመጓዝ ላይ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በመጋጨታቸው መሆኑን የፖሊስ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡