የሀገር ውስጥ ዜና

በጭሮ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

November 12, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

አደጋው የተከሰተው ከሐረር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከመኤሶ ሁሴን ወደ ጭሮ በመጓዝ ላይ ከነበረ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

በመምሪያው የትራፊክ ደኅንነት እና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት እሸቱ እንደገለጹት÷ የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ነው፡፡

በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸው ካለፉት ስምንት ሰዎች በተጨማሪ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ለኦቢኤን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!