ኢትዮጵያ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ አካባቢ የተጎናጸፈች ሀገር በመሆኗ የትኛውንም የፍራፍሬ ዓይነት ማምረት እንችላለን- ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ አካባቢ የተጎናጸፈች ሀገር እንደመሆኗ፣ የትኛውንም የፍራፍሬ ዓይነት ማምረት እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በነባር የፍራፍሬ ዓይነቶች ላይ ያለውን ምርታማነት ማሳደግ እና አዳዲስ ዝርያዎችንም ማምረት ይቻላል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ አካባቢ የተጎናጸፈች ሀገር በመሆኗ የትኛውንም የፍራፍሬ ዓይነት ማምረት እንችላለን ሲሉም አውስተዋል፡፡