Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገነባ የዘይት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ዩኒሰን ዘይት ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
 
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
የፋብሪካው አጠቃላይ ግንባታና ማሽን ተከላ ስራ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነ ሲሆን፥በቀን ከ30 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
 
የዘይት ፋብሪካው አኩሪ አተር፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝና ሌሎች የቅባት እህሎችን በግብዓትነት የሚጠቀም መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
ፋብሪካው የማህበረሰቡን የዘይት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
 
በዩኒሰን ኮርፖሬት ስር የሚገኘው ፋብሪካው አሁን ላይ ከ100 በላይ ቋሚና ከ80 በላይ ለሚሆኑ ጊዜያዊ ሰራተኞች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፥ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
 
በሙሉጌታ ደሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.