በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመልሶ ግንባታ 21 ሚሊየን ብር ለገሱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመልሶ ግንባታ 21 ሚሊየን ብር ለግሰዋል፡፡
በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ÷በድጋፍ አሰባሰብ ማጠቃለያና የምስጋና መርሃ ግብር ላይ የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ የዳያስፖራ አባላትና አደረጃጀቶች የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም÷ በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ላደረጉት ወገናዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰባቸውን ከሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡