Fana: At a Speed of Life!

በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተካፈሉ ሁለት አውሮፕላኖች ተጋጭተው መከስከሳቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2ኛው የዓለም ጦርነት ላይ የተካፈሉ የአሜሪካ ሁለት ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ተጋጭተው መከስከሳቸው ተሰምቷል፡፡

ታሪካዊዎቹ አውሮፕላኖች የተጋጩት በዳላስ ከተማ የዓየር ላይ ትርዒት እያሳዩ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተፈጠረው ድንገተኛ አደጋም የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

የአደጋው መንስኤ አውሮፕላኖቹ ተመሳሳይ የበረራ መሥመር በመከተላቸው መሆኑን መርማሪዎች ቢገልጹም፤ ለምን ለሚለው ጥያቄ ግን እስካሁን መልስ አለመገኘቱን ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡

ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖቹ ተጋጭተው የተከሰከሱት ከዳላስ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዳላስ ኤክስኪዩቲቭ ዓየር መንገድ ውስጥ ነው።

የተከሰተውን አደጋ ተከትሎም ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እያየካሄደ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.