Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪይ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ነገ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አመላክቷል።

በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.