ቻይና እና አሜሪካ ለዓለም ዘላቂ ሰላም ከሌሎች ሀገራት ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው – ሺ ጂንፒንግ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሁለቱ ሃያላን ሀገራት መሪዎች በቡድን 20 አባል ሀገራት 17ኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ኢንዶኔዢያ ባሊ ገብተዋል፡፡
ከስብሰባው በፊትም ሁለቱ መሪዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ከሺ ጂንፒንግ ጋር ሲመክሩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።
በውይይታቸውም ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ሺ ጂንፒንግ ተናግረዋል፡፡
ሺ አክለውም÷ ቤጂንግ እና ዋሺንግተን ለዓለም ዘላቂ ሰላም እና ቀጣይ ተስፋ በትብብር እና በቅርነት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡