Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ምርቶች ለማሳደግ በትብብር እንሠራለን – የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ምርቶች ለማሳደግ በትብብር እንደሚሠሩ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሺንያንግ ሊ ገለጹ፡፡

ሺንያንግ ሊ ÷ የፕሮጀክቱ ተቀዳሚ ዓላማ በኢትዮጵያ ያለውን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ የጥራት ደረጃ ማሳደግ ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በተለይ ከኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራት እንዲጨምር እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማስቀረት በሀገር ውስጥ መተካት እንዲቻል ባሉ በአማራጮች ላይ በትብብር መሥራት እንደሚፈልጉም ነው የጠቆሙት፡፡

በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በተካሄደው የመጀመሪያ ቀን የመክፈቻ መርሐ-ግብር ሁለቱ ወገኖች የፕሮጀክቱን አዋጭነት ለመፈተሽ ቅድመ ዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ ዕቅድ አውጥተዋል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ÷ የኮሪያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ሥር የሠደደ ፣ ታሪካዊ ፣ በወዳጅነት እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ መሆኑን አንስተዋል።

የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከኮሪያው ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ጋር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

መርሐ-ግብሩ በፈረንጆቹ ሕዳር 22 ይጠናቀቃል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.