Fana: At a Speed of Life!

11ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባዔ ነገ ይጀመራል

አዲ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባዔ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎች እና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኤዳኦ አብዲ እንደገለጹት÷ ጉባዔው ከንግድ በዘለለ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ጉባዔው የኢትዮጵያን ላኪዎች፣ አምራቾች፣ ማኅበራት እና ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ከዓለም አቀፍ ሸማቾች ጋር በማገናኘት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የምርት ሃብት ለዓለም ለማስተዋወቅ ያስችላታል መባሉንም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉባዔው ተሳታፊ የውጪ ዜጎች የኢትዮጵያን የመስህብ ሥፍራዎች እንዲጎበኙ ስለሚደረግ ከንግድ ለንግድ ግንኙነት በተጨማሪ ለቱሪዝም እንቅስቃሴው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ ላኪዎች ተወዳድሮ ለማሸነፍ ጥራት ያለው ምርት ማቅረብ ላይ ትኩረትና ዝግጅት እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.