Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ በጊምቦ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ “የሌማት ትሩፋት” መርሐ ግብሮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ “የሌማት ትሩፋት” መርሐ ግብሮችን ጎብኝተዋል፡፡

በአቶ አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጊምቦ ወረዳ በወጣቶች እየተከናወነ የሚገኘውን የዶሮ እርባታ እና በአርሶ አደሮች እየተከናወኑ የሚገኙትን የማርና ሌሎች የግብርና ስራዎችን ነው ተዘዋውሮ የተመለከተው፡፡

በወረዳው እየተከናወነ የሚገኙት የግብርና ስራዎች እንቅስቃሴ ለሌሎች አርዓያ መሆን የሚችሉ “የሌማት ትሩፋት” ስራዎች መሆናቸው ተገልጿል።

በጉብኝቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቀሩ ረጋሳ አንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.