Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ዛሬ ይወጣል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮምን የሚቀላቀለው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆይ ጨረታ ፍላጎቱን እንዲያሳውቅ ገንዘብ ሚኒስቴር ጠየቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል በሚዛወርበት ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻን ወደ ግል ዘርፍ ለማስተላለፍ እና በቴሌ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሚሰማራው ሦስተኛው ኩባንያ ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ መውጣቱን ገልጸዋል፡፡

በዚሁ መሠረት አሁን በሥራ ላይ ያሉትን ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮምን የሚቀላቀለው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ድርጅት÷ በገንዘብ ሚኒስቴር ድረ ገጽ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆይ ጨረታ ፍላጎቱን ማሳወቅ እንደሚችል ተገልጿል።

በቆንጂት ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.