Fana: At a Speed of Life!

ተንቀሳቃሽ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታዳጊዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚሰጠው ተንቀሳቃሽ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል ወይም “ዲጂ ትራክ” አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ እና የሁዋዌ የሰሜን አፍሪካ ዳይሬክተር ሊዮ ሊዮ ተገኝተዋል።

“ዲጂ ትራክ” ለታዳጊዎችና ለወጣቶች መሠረታዊ የኮዲንግ ፣ የፕሮግራሚንግና የሮቦቲክስ ስልጠናዎችን የሚያገኙበት ተንቀሳቃሽ የስልጠና ማዕከል መሆኑ ተመላክቷል።

የስልጠና ማዕከሉን ኤኒ ዋን ካን ኮድ፣ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሁዋዌ ቴክኖሎጂ በትብብር እንደሰሩት ተገልጿል፡፡

ተንቀሳቃሽ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከልሉ በጸሀይ ሃይል የሚሰራ መሆኑ ነው የተጠቆመው ።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.