በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋትን የማስተዋወቅ መርሐ ግብር ተካሔደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በሸበዲኖ ወረዳ በፉራ ቀበሌ የሌማት ትሩፋትን የማስተዋወቅ መርሐ ግብር ተካሔደ፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
መርሐ ግብሩ እንደሀገር የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ለማሳካት የተያዘውን ውጥን ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አቶ ደስታን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሸበዲኖ ተገኝተው÷ የእንስሳትና የአሳ ሀብት፣ የአቮካዶ ምርት፣ የንብ ማነብ፣ የወተት፣ የቡና ልማትና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ ሁለንተናዊ የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡
ክልሉ የማር፣ የዶሮ፣ የወተትና ሌሎች ምርቶችን ለማምረት ምቹ በመሆኑ በሙሉ አቅም መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
የተጀመረውን ውጥን አስፍቶ በማስቀጠል የሌማት ትሩፋት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!