Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት ብድር ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የሦስተኛ ደረጃ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት ለሚችሉ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ሦስተኛ ደረጃ (ተርሸሪ ሌቭል) ሆስፒታል ዘመናዊ መሣሪያዎችን አካቶ የተሟላ አገልግሎት ለታካሚዎች የሚሰጥ ሲሆን÷ ከሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ሆስፒታሎች በሪፈር የሚላኩ ታካሚዎችን ተቀብሎ አገልግሎት የሚሰጥ ጤና ተቋም ነው።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት÷ ባንኩ በርካታ ገንዘብ የሚጠይቁና በውጭ የሚደረጉ የሕክምና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ እንዲጀመሩ ለማስቻል የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና የሚሰጡ ተቋማትን ለመደገፍ ተዘጋጅቷል፡፡

በዘርፉ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀረቡ መኖራቸውን እና ፕሮጀክቱን በቀጣዮቹ አራት ወራት ለማፅደቅ መታቀዱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.