ሚኒስቴሩ ከአምራች ዘርፉ 562 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአምራች ዘርፍ 562 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሮች እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ባለበት ወቅት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት÷ እሴት ጨምሮ ወደ ውጪ መላክ ላይ ያለውን ክፍተት በመሙላት በዘርፉ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ማግኝት ላይ በትኩረት ይሰራል ፡፡
ኢንቨስትመንቶቹ የውጭ ምንዛሬን ከማምጣት ባለፈ እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የዕውቀት ሽግግር ተገኝቶባቸዋል
ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፖርኮች ውስጥ ገብተው ምርቶቻቸውን ወደ ውጪ ከሚልኩት ኢንዱስትሪዎች መካከል የጨርቃ ጨርቅ ድርሻ የላቀ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
ተፈጥሮ የነበረው የውጭ ኢንቨስትመንት መፋዘዝ አሁን ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የታየበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኢንቨስትመንቶቹ የውጭ ምንዛሬን ከማምጣት ባለፈ እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የዕውቀት ሽግግር ተገኝቶባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በኢሳያስ ገላው