Fana: At a Speed of Life!

ሀዲያ ሆሳዕና እና ሐዋሳ ከተማ 2 አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሣምንት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ከሐዋሳ ከተማ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተለያዩ፡፡

የሀዲያ ሆሳዕናን ግቦች÷ ፀጋዬ ብርሃኑ በ25ኛው እና መለሰ ሚሻሞ በ85ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

የሐዋሳ ከተማን ግቦች ደግሞ÷ ሙጂብ ቃሲም በ92ኛው እና ኤፍሬም አሻሞ በ93ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ላይ በሲዳማ ቡና እና በኢትዮጵያ መድን መካከል የተካሔደው ጨዋታ በኢትዮጵያ መድን 4 ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጎሎቹንም÷ ሀብታሙ ሸዋለም በ37ኛው፣ ዮናስ ገረመው በ41ኛው፣ ብሩክ ሙሉጌታ በ48ኛው (በጭማሪ ሰዓት) እና                ኪቲካ ጅማ በ65ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.