የሀገር ውስጥ ዜና

31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ነገ በሐዋሳ ይካሄዳል

By Feven Bishaw

November 17, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ጉባኤ “ጠንካራ የትምህርትና ምዘና ስርአት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

ጉባኤው ነገ እና ከነገ በስቲያ የሚካሄድ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለት ከከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እቅድ አፈፃፀምና አጠቃላይ አካሄድ ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ውይይት እያካሄዱ ነው።

በተጨማሪም በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ ዙሪያም የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው በሁሉም ዘርፎች የትምህርት ዘርፉን አጠቃላይ የእስካሁን ጉዞና የወደፊት አቅጣጫ በጥልቀት ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ