የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል እና የብሄረሰቦች ምክር ቤት የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

By Shambel Mihret

November 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት እና የብሄረሰቦች ምክር ቤት የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልል የዞንና የልዩ ወረዳ የምክር ቤት አባላት በተገኙበት የጋራ ጉባዔው በወላይታ ሶዶ ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምክር ቤቱ በዞንና ልዩ ወረዳዎች ያሉ የምክር ቤት ድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስን እንደሚገመግም ደሬቴድ ዘግቧል፡፡