Fana: At a Speed of Life!

የታይፎይድ መንስዔ፣ምልክቶችና መከላከያ መንገዶች

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይፎይድ የሚከሰተው “ሳልሞኔላ ታይፊ ” በተባለ ባክቴሪያ ሲሆን ባክቴሪያው በተበከለ ምግብ፣ መጠጥ ወይም ውሃ ይተላለፋል።

በሳልሞኔላ ታይፊ የተያዙ ሰዎች ባክቴሪያውን በአንጀታቸውና በደማቸው ውስጥ ይሸከማሉ።

የታይፎይድ በሽታ የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች የሆድ ህመም፣ ትኩሳት እና አጠቃላይ የህመም ስሜት ሲሆኑ እነዚህ የመጀመሪያ ምልክቶች ከሌሎች በሽታዎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

ታይፎይድ ትኩሳት እየተባባሰ ሲሄድ ብዙውን ጊዜ ምልክቶቹ ከፍተኛ ትኩሳት (እስከ 104 ዲግሪ ፋራናይት)፣ራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ የሆድ ድርቀት ቀጥሎም ተቅማጥ ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት እና የድካም ስሜት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሌሎች የታይፎይድ ትኩሳት ምልክቶች ደግሞ ሰገራ ላይ ደም ማየት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ከባድ ድካም፣ ትኩረት የመስጠት ችግር፣ ግራ መጋባት እና ቅዠት መሆናቸውን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

መከላከያ መንገዶቹ ደግሞ እጅን በውሃ እና በሳሙና ቶሎ ቶሎ መታጠብ፣ ውሃን አክሞ መጠቀም፣ ያልበሰሉ ምግቦችን አለመመገብና ምግብን በትኩሱ መመገብ ይጠቀሳሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.