Fana: At a Speed of Life!

በቱም ከተማ ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱም ከተማ ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ነጋሽ ዋጌሾ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ፕሮጀክቱ ረጅም ጊዜ ህብረተሰቡ ሲጠይቅ የነበረውን የውሃ ችግር እንደሚፈታና የሴቶችንና ህፃናትን ድካም እንደሚያቃልል ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ግማሽ ወጪ በብድር ቀሪው ደግሞ በመንግስት ተቋማት መዋጮ የሚሸፈን በመሆኑ ፕሮጀክቱ በጊዜ እንዲጠናቀቅ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በላቸው በበኩላቸው ÷ለፕሮጀክቱ ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግና ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

በተስፋዬ መሬሳ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.