Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከተመድ የሥነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ከተባበሩት መንግስታት የሥነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ሱዛን ማንዶንግ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በሥነ ሕዝብና ልማት ጉዳዮች ዙሪያ የነበረውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው እና ወደፊት በጋራ ሊሰሯቸው ባቀዷቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ  የትኩረት መስክ የሆነውን የሥነ ሕዝብና ልማት ትሩፋት መርሐ ግብር ለማስጀመር የሚያግዝ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ከውይይቱ በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት የሥነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ሱዛን ማንዶንግ  በፕላን ሚኒስቴር ጉብኝት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.