Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል።

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።

10 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የድል ጎሎቹን ዮናታን ኤሊያስ እና ቃል ኪዳን ዘላለም ሲያስቆጥሩ ቦና ዓሊ ደግሞ የአዳማ ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።

ምሽት 1 ሰአት ላይ በተደረገ ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል ተገናኝተው ጨዋታው ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.