የሀገር ውስጥ ዜና

በምእራብ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

March 26, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ ወረዳ ባላሚ በተባለ ከተማ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ላይ ነው የደረሰው።