17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-ፌደሬሽን ም/ ቤት
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ከክልልና ፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
የፌደሬሽን ምክር ቤት 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል አከባበርን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ምክር ቤቱ በመግለጫው÷ 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር አንስቷል፡፡
በዓሉ “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል መቀራረብን፣ አብሮነትንና የጋራ ዕሴትን በሚያጎለብቱ ሁነቶች እንደሚከበር በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ያለአንዳች የጸጥታ ስጋት እንዲከበርም ከክልል እና ከፌዴራል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው፡፡
በሰሎሞን ይታየው እና ወንድሙ አዱኛ