ስፓርት

ሊግ ኩባንያው የቴሌቪዥን መብት የመጀመሪያ ክፍያን ለክለቦች አስረከበ

By Melaku Gedif

November 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2015 ዓ.ም የቴሌቪዥን መብት የመጀመሪያ ክፍያን ለክለቦች መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሳታፊ 16 ክለቦች እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ከሊግ ኩባንያው ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡

የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአጠቃላይ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ በሊግ ኩባንያው ተፈጽሟል፡፡

ክለቦቹ ካገኙት የቴሌቪዥን የመብት ሽያጭ ክፍያ ለኮሚሽነሮችና ዳኞች ክፍያ መፈጸማቸውንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

በወርቅነህ ጋሻሁን