Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ በነበረው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

ለዓመታት በተሠራው የልዩነትና የጥላቻ ፖለቲካ ምክንያት ማንኛውንም በደል ከማንነት ጋር የማያያዝ ልማድ እንዲፈጠር መደረጉ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ይህን አስተሳሰብ ለማሸነፍ በመመካከር መስራት ይገባል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ማንኛውም ችግር መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው ተቀራርቦ በመወያየትና በመመካከር መሆኑም ተገልጿል።

ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ወንጀልን በጋራ መከላከል የሁሉም ነዋሪዎች የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ዚያድ መሀመድ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮምሽን ምክትል ኮሚሽነሮች እና ሌሎች አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.