Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ዋንጫ ዛሬ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በኳታር ይጀመራል።

የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ 60 ሺህ ገደማ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባለው አል በይት ስታዲየም ይካሔዳል፡፡

በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የውድድሩ ሳውንድ ትራክ ተብሎ በፊፋ እውቅና የተሰጠው “ሃያ ሃያ” (አብሮነት ይሻላል) የሚለው ሙዚቃ ይቀርባል፡፡

የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱን ተከትሎ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኳታር ከኢኳዶር የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

ለአንድ ወር ገደማ የሚቆየውን የውድድር መርሐ ግብር 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሕዝብ በስታዲየም ተገኝቶ ጨዋታውን እንደሚመለከት ይጠበቃል፡፡

የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በኳታር አዘጋጅነት ነው የሚካሔደው፡፡

በ2022 የዓለም ዋንጫ አፍሪካ÷ በሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ሞሮኮ፣ ጋና እና ካሜሩን ተወክላ ትሳተፋለች፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.