Fana: At a Speed of Life!

በደጀን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ደጀን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ትላንት ከለሊቱ 6 ሰዓት ከ30 ሲሆን 44 የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ወደ ደቡብ ጎንደር በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የትኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ በጨት ወንዝ አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት በመገልበጡ ነው፡፡

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም 22 ተማሪዎች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የደጀን ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በደጀን ሆስፒታል እንዲሁም በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤው እየተጣራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በሰላም አሰፋ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.