በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተሽከርካሪ ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት ጉዳት አደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተሽከርካሪ ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፓሊስ አስታወቀ፡፡
በዞኑ ጎሮጉቱ ወረዳ ገንዳ ጋራጎላ በተባለ ቀበሌ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-06992 ኢት የሆነ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ ተሸከርካሪ ከነተሳቢው ወደ መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት የአንድ ሠው ህይወት ሲቀጥፍ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንፔክተር ቶሎሳ ጉሹ እንደገለፁት ተሸከርካሪው ከአዲስ አበባ ወደ ጂግጂጋ በመጓዝ ላይ እንዳለ በንጋቱ 12፡30 አካባቢ መንገድ ላይ የነበረን ግለሰብ ገጭቶ አቅራቢያው ወደሚገኙ ሦስት መኖሪያ ቤቶች በመግባት ጉዳት አ ድርሷል፡፡
የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑና በአደጋው የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑንና ጉዳቱን ያደረሰው አሽከርካሪ ለጊዜ ከስፍራው መሰወሩን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በተሾመ ኃይሉ