Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየመከረ ነዉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየመከረ ነው፡፡

ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ነው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየመከረ የሚገኘው፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርኣያ በምክክሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሀገር ሽማግሌዎች ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቱ በሚያጋጥሙ አለመግባባቶች ባህልን፣ ወግን እና እምነትን ባከበረ መልኩ ለሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል፡፡

የሽምግልና ባህል የኢትዮጵያ አንዱ መገለጫ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

አሁን በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመቅረፍ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በምንችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.