ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ዙር ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ በዛሬው እለት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ዜጎቹ ከሳዑዲ መንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት በመጀመሪያው ዙር በተደረጉ 198 በረራዎች ከ71 ሺህ በላይ ዜጎችን መመለስ መቻሉ ተገልጿል።
በዛሬው እለት በተደረጉ 3 በረራዎች ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በበረከት ተካልኝ