የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ 90 ሔክታር መሬት አጥረው የተቀመጡ ባለሀብቶች ውል ተቋረጠ

By ዮሐንስ ደርበው

November 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 90 ሔክታር መሬት ያለምንም አገልግሎት አጥረው የተቀመጡ ባለሀብቶች ውል መቋረጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ቀነዓ ያደታ በሰጡት መግለጫ÷ በአዲስ አበባ መሬት አጥረው ለበርካታ ዓመታት ሳያለሙ በተቀመጡ ባለሃብቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ከመሬት ልማት ጋር በተያያዘ በሚታዩ ችግሮች ላይ እየተወሰዱ ያሉ አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አብራርተዋል፡፡

ለአብነትም እስካሁን በአዲስ አበባ ከከተማ አስተዳደሩ 90 ሔክታር መሬት በሊዝ አዋጁ መሠረት ወስደው ሳያለሙ ለዓመታት አጥረው የተቀመጡ ባለሀብቶች ውል መቋረጡን ገልጸዋል፡፡

ውል የተቋረጠበት 90 ሔክተር መሬት በቅርቡ ለዓልሚዎች ግልጽ ጨረታ እንደሚወጣበትም ጠቁመዋል፡፡

በመሬት ልማትና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮች መለየታቸውን ጠቁመው÷ ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ነው የተናገሩት፡፡

ግንባታ ጀምረው በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ያሉ ዓለሚዎችም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም  ድረስ እንዲያጠናቅቁ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!