Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዋንጫው እንግሊዝ ኢራንን ግማሽ ደርዘን ጎል በማስቆጠር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ቀን የኳታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታ እንግሊዝ ኢራንን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፋለች።

ስምንት ጎሎች ባስተናገደው የምድብ 2 መክፈቻ ጨዋታ እንግሊዝ 6 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆናለች።

በኳታር ካሊፋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለእንግሊዝ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ራሂም ስተርሊንግ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃክ ግሪሊሽ አንዳንድ ጎል ሲያስቆጥሩ፥ ቡካዮ ሳካ ሁለት ጎል አስቆጥሯል።

የኢራንን ሁለት ጎሎች ለፖርቶ የሚጫወተው መሃዲ ታርሚ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ቤሊንግሃም እና ቡካዮ ሳካ ከማይክል ኦውን በመቀጠል በዓለም ዋንጫው በትንሽ እድሜ ለእንግሊዝ ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች በምድብ 1 ሴኔጋል ከኔዘርላንድስ ምሽት አንድ ሰዓት እንዲሁም በምድብ 2 አሜሪካ እና ዌልስ ምሽት 4 ሰአት ይጫወታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.