ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ዓለም ላይ ቀዳሚ ሆናለች

By Tibebu Kebede

March 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ከዓለም ቀዳሚ ሃገር ሆናለች።

አሁን ላይ በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ85 ሺህ በልጧል።

ይህም ዓለም ላይ ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በቻይና 81 ሺህ 340 እንዲሁም በጣልያን 80 ሺህ 589 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

በስፔን በቫይረሱ በአንድ ቀን ብቻ 769 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

እስካሁን ድረስ ዓለም ላይ በቫይረሱ ሳቢያ 24 ሺህ 361 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 124 ሺህ 351 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ