በሶማሌ ክልል ከ28 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በዚህ አመት ከ28 ሚሊየን ኩንታል በላይ የግብርና ምርት ለመሠብሠብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም ለስንዴ ምርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከክልሉ አልፎ ሀገርን መመገብ የሚችል ምርት ለማግኘት ወደ ስራ መገባቱም ነው የተነሳው፡፡
በክልሉ ፋፈን ዞን ቱሊጉሌድ ወረዳም ለምቶ የደረሰው የስንዴ ማሳ አጨዳ ተጀምሯል።
እንዲሁም በዘንድሮው የምርት አመት ብቻ በቱሊ ጉሌድ ወረዳ 83 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት ለአጨዳ ዝግጁ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከ987 ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡