Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሀላባ ዞን እየተካሄደ ነው፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር÷ ክልላዊ የሌማት ቱሩፋትን ፋይዳ አስተዋውቀዋል፡፡

አቶ ኡስማን አያይዘውም በክልሉ ያለውን ፀጋ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

የሌማት ቱሩፋትን እውን ለማድረግ ከወተት፣ ከዶሮ፣ ከስጋና ማር በተጨማሪ የአትክልት፣ የስራስር እና የእንሰት ሰብሎች ሲታከልበት ሌማታችን የተሟላ ይሆናል ነው ያሉት።

በክልሉ የእንስሳትን ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ያሉት ኃላፊው፥ በክልሉ ከወተት ምርታማነት አንጻር በአማካይ ከ14 እስከ 38 ሊትር ወተት ማሳደግ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

ክልሉ ካለው ጸጋ አንጻር ከዶሮ፣ ከስጋ፣ ከወተት፣ ከማር እና ከዓሳ የሚገኘውን ሀብት ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመርሐ ግብሩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.