Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን የገንዘብ ዐቅም ማጠናከር የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ያስችላል – ኢጋድ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሴቶችን የገንዘብ ዐቅም ማጠናከር የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን እና ተሳትፎ ለማጎልበት እንደሚያስችል ኢጋድ አስታወቀ፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት ያስችላል ያለውን የሙከራ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል፡፡

የቀጣናው እናቶች፣ እኅቶች እና ሴት ልጆች “የገንዘብ ዐቅም” ከተጠናከረ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና እንደሚያድግ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ አመላክተዋል፡፡

ለዘላቂ ሰላም እና ልማት ሴቶችን ፤ለማብቃት ቁርጠኛ መሆናቸውንም በመረጃቸው ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.