የአሜሪካ ጦር በደቡባዊ ነጻ የውሃ ቀጠና ኃይሉን እያጠናከረ መምጣቱ ተቀባይነት የለውም – ኢራን
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር ወታደራዊ ኃይሉን በደቡባዊ ነጻ ዓለም አቀፋዊ የውሃ ቀጠና እያጠናከረ መምጣቱ ተቀባይነት እንደሌለው ኢራን አስታወቀች፡፡
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ፥ የአሜሪካ ጦር የአካባቢውን መረጋጋት እና ሠላም ከማደፍረስ ውጪ በቀጣናው መቆየቱ የሚፈይደው ነገር የለም ብለዋል፡፡
ሰላምና መረጋጋትን በዘላቂነት ለማስፈን ብቸኛው አማራጭ የቀጣናውን የባሕር ዳርቻ እና ሀገራት ትብብር ማጠናከር እንደሆነ መናገራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡