Fana: At a Speed of Life!

አብርሆት ቤተ መጻሕፍት እስከ ሌሊት 6 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከነገ ሕዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሌሊት 6 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጸ።
የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ እንዳሉት÷ ቤተ መጻሕፍቱ አንባቢ ትውልድን ለማፍራት ትልቅ ድርሻ ያለው ፣ ታሪክ ሠሪ ትውልድ በንባብ የሚገነባበት ማዕከል ነው።
በንግግርና ውይይት የሚያምን ትውልድ የሚገነባው አንባቢ ትውልድ ሲፈጠር መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
ቤተ መጻሕፍቱ ከዚህ ቀደም ከጧቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሠዓት ብቻ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር አውስተው ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ሰዓት እንዲራዘም በጠየቁት መሰረት እስከ ሌሊት 6 ሠዓት ሊራዘም መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ከጧቱ 2 ሠዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሠዓት ድረስ ቤተ መጻሕፍቱ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.