ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዓለም ዋንጫ ሳዑዲ አርጀንቲናን ማሸነፏን ተከትሎ የሀገሪቱ ንጉስ ነገ የደስታ መግለጫ ብሄራዊ በዓል እንዲሆን አወጁ

By Shambel Mihret

November 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ነገ ረቡዕ የዕረፍት እና የደስታ መግለጫ ቀን ሆኖ እንዲከበር አውጀዋል፡፡

ዐዋጁ የተላለፈው÷ የሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ላይ ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት የነገው ዕለት በመላው ሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች እንዲያርፉ እና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ታውጇል፡፡

ዛሬ ቀን 7 ሰዓት ላይ በተካሔደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሳዑዲ ዓረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ 1 ማሸነፏ ይታወቃል፡፡