የፍትህ ስርዓቱ ከፖለቲካዊ ለውጥ በኋላ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በሚል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ከፖለቲካዊ ለውጥ በኋላ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በሚል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በውይይቱ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮች አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ጉዞ የሚዳስሱ ጥናታዊ ፅሁፎች እየቀረቡ ነው።
የፍትህ ሁኔታ በኢትዮጵያ፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ በዐቃቤ ህግ ላይ የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎች እና ፖሊስና የፍትህ ስርዓቱ አፈፃፀም የሚሉ ጥናታዊ ፅሁፎች እና የግል አስተያየቶችም ቀርበዋል።
በምንይችል አዘዘው