Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ኩባ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ኩባ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የኩባው ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ ከቅዳሜ ጀምሮ በሩሲያ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኩባው አቻቸው ሚጉዌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የመከሩት አሜሪካ በሀገራቱ ላይ በተናጠል የምትጥላቸውን ማዕቀቦች በጥምረት መቋቋም ይችሉ ዘንድ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኩባው አቻቸው ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የኩባ ሕዝብ ለነፃነቱ እና ሉዓላዊነቱ መከበር የሚያደርገውን ትግል ሩሲያ ሁልጊዜም እንደምትደግፍ መግለጻቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ከየትኛውም ወገን በኩባ ላይ የሚጣል ማዕቀብም ሆነ ክልከላ እና እግድ እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በዓለምአቀፍ መድረኮች ላይ ከኩባ ጎን እንደሚቆሙም በውይይታቸው ወቅት ቃል ገብተዋል።

የኩባው ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ፥ ሩሲያ ከሀገራት ጋር በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተቀራርቦ ለመሥራት የምታደርገውን ጥረት እና የምትጫወተውን ግንባር ቀደም ሚና አድንቀዋል፡፡

ኩባ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማሳደግ እንደምትፈልግ እና “ሩሲያ ኩባ ላይ ሁልጊዜም ዕምነቷን ልትጥል እንደምትችል” ነው የገለጹት።

አሜሪካ ሞስኮ ላይ የጣለችውን ማዕቀብም አውግዘዋል።

ሀገራቱ በውይይታቸው ወዳጅነታቸው በመተማመን እና በፅኑ መሠረት ላይ ፀንቶ የሚቀጥል መሆን እንዳለበት መግባባት ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው።

የኩባው ፕሬዚዳንት ከሩሲያ አቻቸው ጋር ከመወያየታቸው አስቀድሞ ሩሲያ ለሟቹ የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ መታሰቢያነት ሞስኮ ላይ ያቆመችውን ሐውልት በይፋ መርቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.